በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ከተረጂነት ወደ ሉዓላዊነት በራስ አቅም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ሲያካሄድ የቆየው የዞን የኢንስፔክሽን ቡድን የድጋፍና ክትትል ስራውን ማጠቃለያ ተገመገመ።
መስከረም፣14/2019(የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን)
ቡድኑ በከተማ አስተዳደሩ በራስ አቅም የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ተረጂነትን ለማስቀረት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እና የዝግጁነት ሁኔታ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ድጋፍና ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።
በክትትል ቆይታውም ከተረጂነት ለመውጣት የተከናወኑ አጠቃላይ ስራዎችን ከመረጃ አደረጃጀት ጀምሮ በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን፣ የተገኙ ጠንካራ ጎኖች እና መሻሻል የሚገባቸው ነጥቦች ላይ ለከተማ አስተዳደሩ አስተባባሪ አካላት ግብረ-መልስ ሰጥቷል።
በመጨረሻም፣ የስልጤ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ መህዲያ ሐምዳላ እና የከተማ አስተዳደሩ አካላት በተገኙበት፤ ከተማ አስተዳደሩና ቀበሌዎች በስኮር ካርድ መሠረት የተመዘኑበት ምዘና ውጤት ማጠቃለያ በከተማ አስተዳደሩ አስተባባሪ ቀርቦ በመገምገም የጋራ በማድረግ መድረኩ ተጠናቋል።